1. ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ።
2. “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ተሰብሰቡና ስሙ፤አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤
3. “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ኀይሌና የጒብዝናዬም መጀመሪያ፤በክብር ትልቃለህ በኀይልምትበልጣለህ።
4. እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅናአይኖርህም፤የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤ምንጣፌንም አርክሰሃል።
5. ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።