ዘፍጥረት 46:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የአሴር ልጆች፦ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤የበሪዓ ልጆች፦ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤

18. እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

19. የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤

20. በግብፅም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።

21. የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌንሑፊምና አርድ ናቸው።

ዘፍጥረት 46