19. እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
20. በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
21. ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
22. የሎጣን ልጆች፦ሖሪና ሔማም፤ የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።
23. የሦባል ልጆች፦ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎና አውናም፤
24. የፅብዖን ልጆች፦አያና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።
25. የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ አህሊባማ፤
26. የዲሶን ልጆች፦ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራንና ክራን፤
27. የኤጽር ልጆች፦ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
28. የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።
29. የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
30. ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
31. ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦
32. የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።