ዘፍጥረት 3:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።

13. እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።

14. እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣“ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉተለይተህ የተረገምህ ሁን፤በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህእየተሳብህ ትሄዳለህ፤ዐፈርም ትበላለህ።

15. በአንተና በሴቲቱ፣በዘርህና በዘሯ መካከል፣ጠላትነትን አደርጋለሁ፤እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”

ዘፍጥረት 3