ዘፍጥረት 2:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. አዳምም እንዲህ አለ፤“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ሥጋም ከሥጋዬ ናት።ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።”

24. ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

25. አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።

ዘፍጥረት 2