ዘፍጥረት 13:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ በሙሉ መርጦ ወደ ምሥራቅ አመራ፤ ሁለቱ ሰዎች በዚሁ ተለያዩ።

12. አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል በሰዶም አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ።

13. የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እጅግ ኃጥኣን ነበሩ።

ዘፍጥረት 13