ዘፀአት 37:27-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ለሸክም የሚሆኑትን መሎጊያዎች ለመያዝ ትይዩ የሆኑ ከክፈፉ ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠሩ።

28. መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ በወርቅም ለበጧቸው።

29. እንዲሁም የተቀደሰውን ቅብዐ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠሩ።

ዘፀአት 37