ዘፀአት 33:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ከዚያም ሙሴ “እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ” አለው።

19. እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ በፊትህም ስሜን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ዐውጃለሁ፤ ለምምረው ምሕረት አደርጋለሁ፤ ለምራራለትም ርኅራኄ አደርጋለሁ፤

20. ነገር ግን፣ ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል፣ ፊቴን ማየት አትችልም።

ዘፀአት 33