ዘፀአት 29:44-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

44. “ስለዚህ የመገናኛው ድንኳንና መሠዊያውን እኔ እቀድሳለሁ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንና ወንድ ልጆቹን እቀድሳለሁ።

45. ከዚያም በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካቸውም (ኤሎሂም) እሆናለሁ።

46. በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ያወጣኋቸው እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላካቸው ነኝ።

ዘፀአት 29