ዘፀአት 29:37-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ለሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ በማድረግ ቀድሰው፤ ከዚያም መሠዊያው እጅግ የተቀደሰ ይሆናል፤ የሚነካውም ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።

38. “በየዕለቱ ያለ ማቋረጥ በመሠዊያው ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ ዓመት የሞላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች፤

39. አንዱን በማለዳ፣ ሌላውን በምሽት አቅርብ።

40. ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር ለውስና ሩብ ኢን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ።

ዘፀአት 29