ዘፀአት 29:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. እነዚህን ሁሉ በአሮንና በወንዶች ልጆቹ እጆች ላይ በማኖር እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዝውዛቸው።

25. ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

26. ለአሮን ክህነት የአውራ በጉን ፍርምባ ከወሰድህ በኋላ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዝውዘው ይህም የአንተ ድርሻ ይሆናል።

ዘፀአት 29