ዘፀአት 29:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርገው ይህ ነው፤ ነውር የሌለባቸው አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ውሰድ፤

2. እርሾ ከሌለው ከምርጥ የስንዴ ዱቄት ቂጣ፣ በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻና በዘይት የተቀባ ኅብስት ጋግር።

3. በሌማት ላይ አድርገህ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር አቅርባቸው።

4. ከዚያም አሮንና ወንድ ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በማምጣት በውሃ እጠባቸው።

5. ልብሶቹን ወስደህ ለአሮን አልብሰው፤ ሸሚዝ፣ የኤፉድ ቀሚስ፣ ኤፉዱንና የደረት ኪሱን አልብሰው፤ ኤፉዱን በእርሱ ላይ በጥበብ በተሠራ መታጠቂያ እሠረው።

ዘፀአት 29