ዘፀአት 28:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. በሁለተኛውም ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤

19. በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤

20. በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጴድ አድርግበት፤ በወርቅ ፈርጥም ክፈፋቸው።

21. የዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስሞች እንደ ማኅተም የተቀረጸባቸው ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይሁኑ።

22. “ለደረት ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ ሆኖ የተጌጠ ጒንጒን አብጅለት።

ዘፀአት 28