ዘፀአት 24:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም ሙሴን “አንተና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ ከሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ጋር ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ኑ፤ ከሩቅም ስገዱ አለው፤

2. ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሊቀርብ የሚችለው ሙሴ ብቻ ነው። ሌሎቹ መቅረብ የለባቸውም ሕዝቡም ከእርሱ ጋር መምጣት የለበትም።”

3. ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃሎችና ሕጎች ሁሉ በነገራቸው ጊዜ በአንድ ድምፅ ሆነው፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” አሉ።

4. ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግሥቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ አሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።

5. ከዚያም ወጣት ወንድ እስራኤላውያንን ላከ፤ እነርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ወይፈኖችን የኅብረት መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሠዉ።

6. ሙሴ የደሙን እኩሌታ ወስዶ በጎድጓዳ ሣህኖች አኖረው፤ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።

ዘፀአት 24