ዘፀአት 21:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ለወንድ ልጁ ትሆን ዘንድ መርጧት ከሆነ እንደ ራሱ ልጅ የሚገባትን መብት ይስጣት።

10. ሌላ ሴት ቢያገባ፣ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧን፣ ልብሷንና የጋብቻ መብቷን አይከልክላት።

11. እነዚህን ሦስት ነገሮች የማያሟላላት ቢሆን፣ ያላንዳች የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ይኖርባታል።

ዘፀአት 21