ዘፀአት 20:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤

2. “ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ ኤሎሂም) እኔ ነኝ።”

3. “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።

4. “በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ካለው ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች በማናቸውም ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ።

ዘፀአት 20