ዘፀአት 15:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ሕዝብህእስከሚያልፉ ድረስ፣የተቤዠኻቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤በክንድህ ብርታት፣እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።

17. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ማደሪያህእንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም።

18. እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”

ዘፀአት 15