15. ፈርዖን እኛን አለቅም ብሎ ልቡን ባደነደነ ጊዜ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን ሁሉ እግዚአብሔር (ያህዌ) ገደለው። እንግዲህ በመጀመሪያ የእናቱን ማሕፀን የከፈተውን ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምሠዋውና የልጆቼ በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ የምዋጀው በዚህ ምክንያት ነው።
16. እግዚአብሔር (ያህዌ) በኀያል ክንዱ እኛን ከግብፅ ያወጣን ስለ ሆነ ይህ ሥርዐት በእጅህም ሆነ በግንባርህ ላይ እንደ ምልክት ይሆናል።”
17. ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አቋራጭ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በፍልስጥኤም ምድር በሚያልፈው መንገድ አልመራቸውም “ጦርነት ቢያጋጥማቸው ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብፅ ይመለሱ ይሆናል” ብሎአልና።