1. ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦
2. ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣
3. ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
4. ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።
5. የያዕቆብ ዘር ጠቅላላ ብዛት ሰባ ሲሆን፣ ዮሴፍ ግን ቀደም ብሎ በግብፅ ነበረ።
6. ከጊዜ በኋላ ዮሴፍና ወንድሞቹ ያም ትውልድ በሙሉ ሞቱ፤
7. ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እየተዋለዱ በዙ፤ ቍጥራቸው እጅግ ከመጨመሩም የተነሣ የግብፅን ምድር ሞሏት።
8. በግብፅም፣ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ነገሠ።
9. እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤