ዘዳግም 6:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።

4. እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችንእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አንድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።

5. አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።

ዘዳግም 6