13. አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል፤ በስሙም ማል።
14. በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት አትከተል፤
15. ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቀናተኛ አምላክ (ኤሎሂም) ስለ ሆነ፣ በአንተም ላይ ቊጣው ስለሚነድ፣ ከምድር ገጽ ያጠፋሃል።
16. በማሳህ እንዳደረጋችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አትፈታተኑት።
17. አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ መመሪያዎችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ።
18. መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤
19. እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።