ዘዳግም 4:47-49 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን፣ የእርሱን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የዐግን፣ የሁለቱን አሞራውያን ነገሥታት ምድር ርስት አድርገው ወሰዱ።

48. ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሴዎን ተራራ ማለትም እስከ አርሞንዔም የሚደርስ ሲሆን፣

49. በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን ዓረባን በሙሉና ከፈስጋ ተረተር በታች ያለውን የዓረባ ባሕር ያጠቃልላል።

ዘዳግም 4