3. በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው።ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤
4. ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፣የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።
5. የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፣በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።
6. “ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤የወገኖቹ ቊጥርም አይጒደልበት።”
7. ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ወደ ወገኖቹም አምጣው።በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!
8. ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦“ቱሚምህና ኡሪምህ፣ለምትወደው ሰው ይሁን፤ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።