1. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰጠው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው፤
2. እንዲህም አለ፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሲና መጣ፤በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤በስተ ቀኙ የሚነድ እሳት ነበር።
3. በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው።ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤