ዘዳግም 32:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣በእስራኤል ልጆች ቊጥር ልክ፣የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤

9. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።

10. እርሱን በምድረ በዳ፣ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።

11. ንስር ጎጆዋን በትና፣በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣

ዘዳግም 32