ዘዳግም 32:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።

8. ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣በእስራኤል ልጆች ቊጥር ልክ፣የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤

9. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።

10. እርሱን በምድረ በዳ፣ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።

ዘዳግም 32