ዘዳግም 32:40-48 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ለዘላለምም ሕያው እንደሆንሁ እናገራለሁ፤

41. የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።

42. ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፣ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች፣የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።”

43. አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ጠላቶቹንም ይበቀላል።ምድሪቱንና ሕዝቡን ይቤዣቸዋልና።

44. ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃሎች በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ።

45. ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣

46. እንዲህ አላቸው፤ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው፣ እኔ ዛሬ በግልጥ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ።

47. ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃሎች አይደሉም፤ በእነርሱ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፤ በምትወር ሷትም ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።

48. በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

ዘዳግም 32