ዘዳግም 32:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም (ኤሎሂም) እርሱ ነው።

5. በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።

6. አንተ ተላላና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን?አባትህ ፈጣሪህ፣የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን?

7. የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።

ዘዳግም 32