ዘዳግም 32:37-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ?

38. የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፣የመጠጥ ቊርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው?እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ!እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ!

39. “እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።

ዘዳግም 32