ዘዳግም 32:30-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ካልተዋቸው በቀር፣አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል?ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደርጋሉ?

31. የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም።

32. ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው።

33. ወይናቸው የእባብ መርዝ፣የመራዥ እባብም መርዝ ነው።

34. “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?

35. በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”

36. ኀይላቸው መድከሙን፣ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ለአገልጋዮቹም ይራራል።

37. እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ?

ዘዳግም 32