3. ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፣
4. ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን ዐንገት ይስበሩ፤
5. እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጒዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።
6. ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፣ በሸለቆው ውስጥ፣ ዐንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ።