ዘዳግም 21:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. “ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው” ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው።

21. ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።

22. አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፤

23. በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ፣ በዚያኑ ዕለት ቅበረው።

ዘዳግም 21