32. ሴዎንና መላው ሰራዊቱ በያሀጽ ጦርነት ሊገጥሙን በወጡ ጊዜ፣
33. አምላካችን እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጃችን ላይ ጣለው፤ እኛም፣ እርሱን ከወንድ ልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋር አንድ ላይ መታነው።
34. በዚያን ጊዜ ከተሞቹን በሙሉ ወስደን የሚኖሩባቸውን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆቻቸውን ጭምር ፈጽመን አጠፋናቸው፤ አንዳቸውንም በሕይወት አላስቀረንም።
35. ከብቶቻቸውንና ከየከተሞቻቸው ያገኘነውን ምርኮ ግን ለራሳችን አደረግን።