17. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።
18. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።
19. ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጒቦም አትቀበል፤ ጒቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።
20. በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።
21. ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም።
22. አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።