ዘዳግም 11:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ውደድ፤ ግዴታውን፣ ሥርዐቱን፣ሕጉንና ትእዛዙን ሁል ጊዜ ጠብቅ።

2. የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ተግሣጽ ይኸውም ግርማውን፣ ብርቱ እጁንና የተዘረጋች ክንዱን ያዩትና የተለማመዱት ልጆቻችሁ ሳይሆኑ እናንተ እንደሆናችሁ ዛሬ አስታውሱ፤

ዘዳግም 11