ዘካርያስ 2:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤

2. እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት።እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋትምን ያህል እንደሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።

3. ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤

4. እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤

5. እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’

ዘካርያስ 2