ዘኁልቍ 7:52-55 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

53. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

54. በስምንተኛው ቀን የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍደሱር ልጅ ገማልኤል ስጦታውን አመጣ፤

55. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

ዘኁልቍ 7