ዘኁልቍ 7:34-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

35. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

36. በአምስተኛው ቀን የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ስጦታውን አመጣ፤

37. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

38. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

ዘኁልቍ 7