ዘኁልቍ 7:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በመጀመሪያው ቀን ስጦታውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፤

13. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

14. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

15. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

16. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

ዘኁልቍ 7