ዘኁልቍ 35:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. “ ‘ሆኖም ተከሳሹ ሰው ሸሽቶ ከተጠጋበት መማጸኛ ከተማ ክልል ከወጣ፣

27. ደም ተበቃዩም ከከተማው ውጭ ካገኘው፣ ተከሳሹን ሊገድለው ይችላል፤ በነፍሰ ገዳይነትም አይጠየቅም።

28. ተከሳሹም ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛው ከተማ ይቈይ፤ ወደ ገዛ ርስቱ መመለስ የሚችለው ከሊቀ ካህናቱ ሞት በኋላ ብቻ ነው።

ዘኁልቍ 35