20. አንድ ሰው አስቦበት ሌላውን በክፋት ገፍትሮ ቢጥለው ወይም እንዲሞት ሆን ብሎ አንዳች ነገር ቢወረውርበት
21. ወይም ደግሞ በጥላቻ ተነሣሥቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት፣ ያ ሰው በሞት ይቀጣል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም መላሹም ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይግደለው።
22. “ ‘ነገር ግን በጥላቻ ሳይሆን እንዲያው በድንገት አንዱ ሌላውን ገፍትሮ ቢጥለው ወይም ሳያስበው አንዳች ነገር ቢወረውርበት
23. ወይም መግደል የሚችል ድንጋይ ሳያይ ጥሎበት ቢሞት፣ ጠላቱ ስላልሆነና ሊጐዳውም አስቦ ያላደረገው ስለ ሆነ፣
24. ማኅበሩ በዚህ ሰውና በደመኛው መካከል በእነዚህ ደንቦች መሠረት ይፍረድ።