ዘኁልቍ 35:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከኢያሪኮለ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

2. “ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞች እንዲሰጧቸው እስራኤላውያንን እዘዛቸው፤ በየከተሞቹ ዙሪያም የግጦሽ መሬት ሰጧቸው።

3. ከተሞቹ ለእነርሱ መኖርያ፣ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻቸውና ለሌሎቹም እንስሶቻቸው ይሆናሉ።

4. “በየከተሞቹ ዙሪያ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸውም የግጦሽ መሬት ከከተማው ቅጥር አንድ ሺህ ክንድ ይዘረጋል።

5. ከዚያም ከተማውን መካከል በማድረግ ወደ ምሥራቅ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ደቡብ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ምዕራብ ሁለት ሺህ ክንድ፣ ወደ ሰሜን ሁለት ሺህ ክንድ ከከተማው ውጭ ለካ፤ እነዚህንም ቦታዎች ለከተሞቹ የግጦሽ መሬት ያደርጓቸዋል።

ዘኁልቍ 35