ዘኁልቍ 33:39-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

39. አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር።

40. በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።

41. እነርሱም ከሖር ተራራ ተነሥተው በሴልሞና ሰፈሩ።

42. ከሴልሞና ተነሥተው በፋኖን ሰፈሩ።

43. ከፋኖን ተነሥተው በአቦት ሰፈሩ።

ዘኁልቍ 33