ዘኁልቍ 31:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፤

2. “ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን ተበቀልላቸው፤ ከዚያም ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ” አለው።

3. ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ምድያማውያንን ለመውጋት እንዲሄዱና ስለ እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲበቀሏቸው ከሰዎቻችሁ ጥቂቶቹን ለጦርነት አዘጋጁ።

4. ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።”

5. ስለዚህ ከእስራኤል ጐሣዎች ተወጣጥቶ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሺህ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ለጦርነት ተዘጋጀ።

ዘኁልቍ 31