ዘኁልቍ 3:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የሜራሪ ጐሣዎች፤ሞሖሊና ሙሲ።እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው።

21. የሎቤናና የሰሜአ ጐሣዎች ከጌርሶን ወገን ናቸው፤ እነዚህ የጌርሶን ጐሣዎች ነበሩ።

22. አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኖአቸው የተቈጠሩት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበር።

23. የጌርሶን ጐሣዎች በምዕራብ በኩል ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ይሰፍራሉ።

ዘኁልቍ 3