28. ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
29. “ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
30. ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።
31. ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
32. “ ‘በሰባተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።