ዘኁልቍ 29:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. “ ‘በአራተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

24. ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተደነገገው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

25. ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

26. “ ‘በአምስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

ዘኁልቍ 29