1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
2. “ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሰኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቊርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ’ በላቸው።
3. ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ።