ዘኁልቍ 27:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ።

9. ሴት ልጅ ከሌለችው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ስጡ።

10. ወንድሞች ከሌሉትም ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ።

11. አባቱ ወንድሞች ከሌሉትውርሱ ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይሰጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”

12. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በዓባሪም ሸንተረር ላይ ወዳለው ወደዚህ ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን ምድር እይ።

ዘኁልቍ 27