ዘኁልቍ 26:59-63 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

59. ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብፅ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።

60. አሮንም የናዳብና የአብዮድ፣ የአልዓዛርና የኢታምር አባት ነበር።

61. ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ።

62. አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺህ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ አብረዋቸው አልተቈጠሩም።

63. ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ካለው ከሞዓብ ሜዳ ላይ የእስራኤልን ሕዝብ በቈጠሩበት ወቅት የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው።

ዘኁልቍ 26